የተረሳ ግርማ
ባለ ቱባ ታሪክ - የሊቃዉንት አንባ - ዉዲቷ ሀገሬ
የሚያስባት አጣች - ሆነች ያዉሬ ጎሬ::
ናቡከደነጾር
ሳያዘምትባት ጦር
ባቢሎን ሳይመታት
ድል አርጎ አንበርክኮ - እጆችዋን ሳይይዛት
እንደ እየሩሳሌም - ኦናነት ጸናባት።
ስልጣኔው አልፏል - ተረት ወሬ ሆኗል
ግርማዋ ተቀብሮ - አሸዋ ዉስጥ አድሮ - ትቢያ ተከናንቧል
የኔ እሚላት አጥታ - አምዶቿ ፈረሱ
ልጆቿም እንዳባይ - ወደ ውጪ ፈሰሱ።
ታህሳስ 1996
አዲሱ አበበ
No comments:
Post a Comment