Sunday, November 28, 2010

የተረሳ ግርማ

የተረሳ ግርማ

ለ ቱባ ታሪክ  -  የሊቃዉንት አንባ   -   ዉዲቷ ሀገሬ
የሚያስባት አጣች  -  ሆነች ያዉሬ ጎሬ::

ናቡከደነጾር
ሳያዘምትባት ጦር
ባቢሎን ሳይመታት
ድል አርጎ አንበርክኮ  -  እጆችዋን ሳይይዛት
እንደ እየሩሳሌም  -  ኦናነት ጸናባት።

ስልጣኔው አልፏል  -  ተረት ወሬ ሆኗል
ግርማዋ ተቀብሮ   -  አሸዋ ዉስጥ አድሮ  -   ትቢያ ተከናንቧል
የኔ እሚላት አጥታ  -  አምዶቿ ፈረሱ
ልጆቿም እንዳባይ  -  ወደ ውጪ ፈሰሱ።

ታህሳስ 1996
አዲሱ አበበ